ኢሳይያስ 28:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ለተረፈው ሕዝቡ፣ የክብር ዘውድ፣ የውበትም አክሊል ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የሠራዊት አምላክ ከሞት ለተረፉት ሕዝቡ የክብር አክሊል ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለተረፉት ሕዝቡ የክብር የተጐነጐነ ዘውድና የተስፋ አክሊል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፥ |
ለጻድቁ ክብር ይሁን የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፦ ከሳሁ፥ ከሳሁ፥ ወዮልኝ! ከሀዲዎች ክህደትን ፈጽመዋል፤ ከሀዲዎች አስከፊ ክህደት ፈጽመዋል አልሁ።
ከዚያ በኋላ ጌታ የዘለዓለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽም ይሆናልና በቀን ብርሃንሽ ፀሐይ መሆኑ ይቀራል፤ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አያስፈልግሽም።