La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 43:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍም ወደ ቤቱ ሲገባ ያመጧቸውን እጅ መንሻዎች አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሴፍም ወደ ቤቱ ሲገባ ያመጧቸውን እጅ መንሻዎች አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሴፍ ወደ ቤት በገባ ጊዜ፥ እርሱ ወዳለበት ክፍል ገብተው ያመጡትን ስጦታ አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴ​ፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእ​ጃ​ቸው ያለ​ውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው ሰገ​ዱ​ለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለው እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 43:26
11 Referencias Cruzadas  

አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”


እርሱም ከፊታቸው ቀደመ፥ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።


በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፥ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።


ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ከርቤ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።


እነርሱም መልሰው፥ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው በአክብሮት እጅ ነሡት።


በፊቱም የኢትዮጵያ ሰዎች ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።


ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፥ ሰገደም፥ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ደኅንነታቸውን ተጠያየቁ፥ ወደ ድንኳኑም ገቡ።


“እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል ጌታ፤ “ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ልሳንም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤” ተብሎ ተጽፎአልና።