Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 14:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል ጌታ፤ “ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ልሳንም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤” ተብሎ ተጽፎአልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ “ ‘እኔ ሕያው ነኝና’ ይላል ጌታ፤ ‘ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይመሰክራል።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ምክንያቱም፦ “እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር፤ ሰው ሁሉ በጒልበቱ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ በአንደበቱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይመሰክራል” ተብሎ ተጽፎአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕል​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይሰ​ግ​ዳል፤ አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይገ​ዛል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እኔ ሕያው ነኝ፥ ይላል ጌታ፥ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 14:11
15 Referencias Cruzadas  

ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።


ምክንያቱም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፥ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ፤


ዓይንሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፥ እንደ ሙሽራም ትጎናጸፊአቸዋለሽ፥ ይላል ጌታ።


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚመሰክር ሁሉ፥ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።


አሕዛብ ስለ ምሕረቱ እግዚአብሔርን እንዲያከብሩት፥ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ፤” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


ስለዚህ በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤


ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የጌታ ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።


አራቱም ሕያዋን ፍጡራን “አሜን” አሉ፤ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።


ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህም አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ይሆናሉ፥ አረም እንደ ዋጠው ስፍራና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘለዓለምም ይጠፋሉ፤ የሕዝቤም ትሩፍ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።


ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።


እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤


“እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ የማኅተም ቀለበት ቢሆን ኖሮ እንኳ፥ ከዚያ አውልቄ እጥልህ ነበር፥ ይላል ጌታ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios