ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፥ እነሆ ባርኬዋለሁ፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፥ ዐሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።
ዘፍጥረት 25:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትውልዳቸው ቅደም ተከተል የተዘረዘሩት የእስማኤል የልጆቹ ስም እንዲህ ነው፥ የእስማኤል የበኩር ልጁ ነባዮት፥ እና ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስማኤል ልጆች ስም እንደ ዕድሜያቸው ቅደም ተከተል እንዲህ ነው፦ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውና በየትውልዳቸው እንዲህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውን በየትውልዳቸው እንዲህ ነው፤ የእስማኤል የበኵር ልጁ፥ |
ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፥ እነሆ ባርኬዋለሁ፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፥ ዐሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።
ዔሳው ወደ እስማኤል ሄደ፥ ማዕሌትንም በፊት ካሉት ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ፥ እርሷም የአብርሃም ልጅ የሆነ የእስማኤል ልጅና የነባዮት እኅት ናት።
ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፥ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።
የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።
እርሱም “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጉትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጉትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።