ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
ዕዝራ 2:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበር ጠባቂዎች ልጆች፦ የሻሉም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጣልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሾባይ ልጆች፥ ሁሉ አንድ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎቹ፦ የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 139 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበረኞች ልጆች፥ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሰበዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበረኞች ልጆች፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጢልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። |
ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አዛዦች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር።
በር ጠባቂዎች፥ የሻሉም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጣልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሾባይ ልጆች፥ አንድ መቶ ሠላሳ ስምንት።