ሕዝቅኤል 45:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ሃያ ቤቶችም ለእነርሱ ርስት ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ስፋት ያለው ስፍራ መኖሪያ ከተሞቻቸውን እንዲከትሙ በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ ሌዋውያን ርስት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀሪው አጋማሽ ማለትም ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱ ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነው ቦታ ደግሞ በቤተ መቅደስ ለሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎት ለተመደቡት ሌዋውያን ርስት ይሆናል፤ ለእነርሱ መኖሪያ የሚሆኑ ከተሞችም በዚያ ይሠራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርዝመቱም ሃያ አምስት ሺህ፥ ወርዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን መኖሪያ ርስት ከሃያ ዕቃ ቤቶች ጋር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ዕፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ለሚቀመጡባቸውም ከተሞች ለራሳቸውም የርስት ይዞታ ይሆናል። |
ይህም ለካህናቱ የተቀደሰ መባ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል። የጌታ መቅደስም በመካከሉ ይሆናል።
ለሌዋውያኑ በካህናቱ ድንበር አጠገብ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ይሆናል፥ ርዝመቱ ሁሉ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል።
መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ የተቀደሰውን መባ ከከተማይቱ ድርሻ ጋር አራት ማዕዘን አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ።