ሕዝቅኤል 45:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከምድሪቱም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል፤ ጌታን ሊያገለግሉ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል፥ ስፍራውም ለቤቶቻቸው መስሪያና ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ይህም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚያገለግሉና፣ በእግዚአብሔር ፊት ለአገልግሎት ለሚቀርቡ ካህናት፣ ቅዱስ የሆነ የምድሪቱ ክፍል ይሆናል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ይህ ከጠቅላላው መሬት የተቀደሰ ክፍል ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ቀርበው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚያገለግሉት ካህናት የተደለደለ ነው፤ ቦታውም ለካህናቱ መኖሪያና ለቤተ መቅደሱ መሥሪያ ይሆናል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከምድርም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል፤ እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል፤ ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ፥ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ከምድርም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል፥ እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል፥ ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል። Ver Capítulo |