ሕዝቅኤል 48:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ይህም ለካህናቱ የተቀደሰ መባ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል። የጌታ መቅደስም በመካከሉ ይሆናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ይህ ለካህናቱ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይቆማል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ካህናቱም ከዚህ ከተቀደሰው ቦታ የተወሰነ ድርሻ ይኖራቸዋል፤ እርሱም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ከሰሜን እስከ ደቡብ ዐሥር ሺህ ክንድ ወርድ ይኖረዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም በመካከሉ ይኖራል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 የመቅደሱም ቀዳምያት ለካህናቱ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በምሥራቅም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደቡብም በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል። የእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ለእነዚህም ለካህናቱ የተቀደሰ መባ ይሆናል፥ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በምሥራቅም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በደቡብም በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል። የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። Ver Capítulo |