Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 48:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለሌዋውያኑ በካህናቱ ድንበር አጠገብ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ይሆናል፥ ርዝመቱ ሁሉ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ከካህናቱም ምድር ጐን ለጐን ሌዋውያኑ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ርዝመትና ዐሥር ሺሕ ክንድ ወርድ ያለው ይዞታ ይኖራቸዋል፤ ጠቅላላ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱም ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከካህናቱ ቦታ ጐን ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ዐሥር ሺህ ክንድ ወርድ የሆነ የሌዋውያን ድርሻ አለ፤ ጠቅላላውም ከካህናቱ ድርሻ ጋር ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ኻያ ሺህ ክንድ ወርድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በካ​ህ​ና​ቱም ድን​በር አቅ​ራ​ቢያ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሆ​ናል፤ ርዝ​መቱ ሁሉ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በካህናቱም ድንበር አንጻር ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ለሌዋውያን ይሆናል፥ ርዝመቱ ሁሉ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 48:13
8 Referencias Cruzadas  

ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ።


ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ሃያ ቤቶችም ለእነርሱ ርስት ይሆናሉ።


በዚያው ክልል ደግሞ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ትለካለህ፤ በእርሱም ውስጥ ቅድስተ ቅዱሳን የሆነ መቅደስ ይሆናል።


በምድርም ላይ በምትኖርበት ጊዜ ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትለው ተጠንቀቅ።”


ከምድሪቱ መባ የተቀደሰው መባ ለእነርሱ ይሆናል፥ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል፤ በሌዋውያን ድንበር አጠገብ ይሆናል።


ለጌታ የተቀደሰ ስለሆነ ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡም፥ የምድሪቱንም በኵራት ወደ ሌላ አይተላለፍም።


የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ ጌታ አምላክህ ቤት አምጣ፤ ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።


በከተማቸውም ዙሪያ ያለው መሰማሪያ የዘለዓለም ርስታቸው ነውና አይሸጥም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios