ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤
2 ሳሙኤል 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለባቸው። እንዲሁም የሠራዊታቸውን አዛዥ ሾባክን አቁስሎት ስለ ነበር እዚያው ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለባቸው። እንዲሁም የሰራዊታቸውን አዛዥ ሶባክን አቍስሎት ስለ ነበር፣ እዚያው ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ሶርያውያንን መልሰው አሳደዱአቸው፤ ዳዊትና ሠራዊቱ ሰባት መቶ የሶርያውያንን ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደሉ፤ እንዲሁም የጠላት ሠራዊት አለቃ የነበረውን ሾባክን መተው አቊስለውት ስለ ነበር እዚያው በጦር ሜዳው ላይ ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት መቶ ሰረገለኞችን፥ አርባ ሺህም ፈረሰኞችን ገደለ፤ የሠራዊቱንም አለቃ ሶቤቅን መታ፤ እርሱም በዚያ ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፥ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት መቶ ሰረገለኞች አርባ ሺህም ፈረሰኞች ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሶባክን መታ፥ እርሱም በዚያ ሞተ። |
ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤
ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችና ሃያ ሺህ እግረኞች ማረከበት። ቁጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።
የሽፍቶች አለቃ ሆኖ ነበር፤ ይህም የሆነው ዳዊት ሀዳድዔዜርን ድል ነሥቶ የእርሱ ጦር ተባባሪዎች የሆኑትን ሶርያውያንን ከፈጀ በኋላ ነበር፤ ረዞንና ተከታዮቹም ወደ ደማስቆ ሄዱ፤ በዚያም ሲኖሩ እርሱን የሶርያ ንጉሥ እንዲሆን አደረጉት።
ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት ሺህ ሰረገለኞች፥ አርባ ሺህም እግረኞች ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሾፋክን ገደለ።
ስለዚህም ጌታ በሐጾር ሆኖ ይገዛ ለነበረው ለከነዓን ንጉሥ ለያቢን አሳልፎ ሰጣቸው። የያቢን ሠራዊት አዛዥ፥ በሐሮሼትሐጎይም የሚኖረው ሲሣራ ነበረ።
ባራቅ ሲሣራን በመከታተል ላይ ስለ ነበር ከዚያ ሲደርስ፥ ያዔል ከድንኳኗ ወጥታ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው፤ ስለዚህ ከእርሷ ጋር ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ ሲሣራም በጆሮ ግንዱ ላይ ካስማ እንደ ተመታበት ሞቶ ተዘርሮ ነበረ።
እጅዋን ወደ ካስማ፥ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፥ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፥ ራሱንም ቸነከረች፥ ጆሮግንዱንም በሳች፥ ጎዳችውም።