መሳፍንት 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ባራቅ ሲሣራን በመከታተል ላይ ስለ ነበር ከዚያ ሲደርስ፥ ያዔል ከድንኳኗ ወጥታ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው፤ ስለዚህ ከእርሷ ጋር ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ ሲሣራም በጆሮ ግንዱ ላይ ካስማ እንደ ተመታበት ሞቶ ተዘርሮ ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ባርቅ ሲሣራን በመከታተል ላይ ስለ ነበር ከዚያ ሲደርስ፣ ኢያዔል ከድንኳኗ ወጥታ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው፤ ስለዚህ ከርሷ ጋራ ወደ ድንኳኗ ገባ፤ ሲሣራም በጆሮ ግንዱ ላይ ካስማ እንደ ተመታበት ሞቶ ተዘርሮ ነበረ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ባራቅ ሲሣራን እያሳደደ ሲመጣ ያዔል ልትቀበለው ወጥታ “ወደዚህ ና! አንተ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። ስለዚህም ከእርስዋ ጋር ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ የድንኳኑ ካስማ በሲሣራ ጆሮ ግንድ ላይ እንደ ተቸነከረ ሬሳውን በመሬት ላይ ተጋድሞ አየ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 እነሆም፥ ባርቅ ሲሣራን ሲያባርር ኢያዔል ልትገናኘው ወጥታ፥ “ና፤ የምትሻውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። ወደ እርስዋም ገባ፤ እነሆም፥ ሲሣራን ወድቆ፥ ሞቶም አገኘው፤ ካስማውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ነበረ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 እነሆም፥ ባርቅ ሲሣራን ሲያባርር ኢያዔል ልትገናኘው ወጥታ፦ ና የምትሻውንም ሰው አሳይሃለሁ አለችው። ወደ እርስዋም ገባ፥ እነሆም፥ ሲሣራን ወድቆ ሞቶም አገኘው፥ ካስማውም ከጆሮግንዱ ውስጥ ነበረ። Ver Capítulo |