Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 10:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለባቸው። እንዲሁም የሰራዊታቸውን አዛዥ ሶባክን አቍስሎት ስለ ነበር፣ እዚያው ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለባቸው። እንዲሁም የሠራዊታቸውን አዛዥ ሾባክን አቁስሎት ስለ ነበር እዚያው ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እስራኤላውያን ሶርያውያንን መልሰው አሳደዱአቸው፤ ዳዊትና ሠራዊቱ ሰባት መቶ የሶርያውያንን ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደሉ፤ እንዲሁም የጠላት ሠራዊት አለቃ የነበረውን ሾባክን መተው አቊስለውት ስለ ነበር እዚያው በጦር ሜዳው ላይ ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት መቶ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ገደለ፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶቤ​ቅን መታ፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፥ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት መቶ ሰረገለኞች አርባ ሺህም ፈረሰኞች ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሶባክን መታ፥ እርሱም በዚያ ሞተ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 10:18
10 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ። ዳዊትም ሰባት ሺሕ ሠረገለኞችና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለ። የሰራዊታቸው አዛዥ ሾፋክም በጦርነቱ ላይ ሞተ።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ


እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው፤ ከእግሬም ሥር ወደቁ።


ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኞችና ሃያ ሺሕ እግረኞች ማረከበት። ቍጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ።


እጇ ካስማ ያዘ፤ ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤ ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤ ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው።


ባርቅ ሲሣራን በመከታተል ላይ ስለ ነበር ከዚያ ሲደርስ፣ ኢያዔል ከድንኳኗ ወጥታ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው፤ ስለዚህ ከርሷ ጋራ ወደ ድንኳኗ ገባ፤ ሲሣራም በጆሮ ግንዱ ላይ ካስማ እንደ ተመታበት ሞቶ ተዘርሮ ነበረ።


ስለዚህም እግዚአብሔር በአሦር ሆኖ ይገዛ ለነበረው ለከነዓን ንጉሥ ለኢያቢስ አሳልፎ ሸጣቸው። የኢያቢስ ሰራዊት አዛዥ፣ በአሪሶት ሐጎይም የሚኖረው ሲሣራ ነበረ፤


ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ መላውን እስራኤልን ሰብስቦ፤ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ኤላም ሄደ።


ዳዊት የሱባን ኀይል በደመሰሰ ጊዜ፣ ሬዞን ሰዎቹን በዙሪያው አሰባስቦ የወንበዴ አለቃ ሆነ፤ ሰዎቹም ወደ ደማስቆ ሄደው ተቀመጡ፤ በዚያም አነገሡት።


ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው። ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios