እናቱ ከዳን ልጆች ናት፥ አባቱም የጢሮስ ሰው ነው፤ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ድንጋይንና እንጨቱን፥ ሐምራዊውንና ሰማያዊውን ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ ለመሥራት፥ ቅርጽም ለመሥራት ንድፍም ለመንደፍ ሌላም ነገር ሁሉ ለማድረግ እውቀት አለው፥ እርሱም ከብልሃተኛዎችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር አብሮ ይሁን።
2 ዜና መዋዕል 26:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚቀመጡትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች ሠራ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ አገር ድረስ ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌምም፣ ንድፎቻቸው በባለሙያዎች የተዘጋጁ፣ በመጠበቂያ የግንብ ማማዎችና በየማእዘኑ መከላከያዎች ላይ ፍላጻ የሚስፈነጠርባቸውንና ትልልቅ ድንጋዮች የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አሠራ። እስኪበረታም ድረስ በሚያስደንቅ ሁኔታ ስለ ታገዘ፣ ዝናው በርቀትና በስፋት ተሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዖዝያ በኢየሩሳሌም በእጅ ሥራ ጥበብ የሠለጠኑ ሰዎች ከመጠበቂያ ግንቦችና ከከተማይቱ ቅጽር ማእዘኖች ላይ ፍላጻዎችንና ታላላቅ ድንጋዮችን የሚያስፈነጥሩ መሣሪያዎችን እንዲሠሩ አደረገ፤ እግዚአብሔር ስለ ረዳውም እጅግ በረታ፤ እጅግም ገናና ሆነ፤ ዝናውም በሁሉ ስፍራ ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን ፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና የመሣሪያዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ። |
እናቱ ከዳን ልጆች ናት፥ አባቱም የጢሮስ ሰው ነው፤ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ድንጋይንና እንጨቱን፥ ሐምራዊውንና ሰማያዊውን ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ ለመሥራት፥ ቅርጽም ለመሥራት ንድፍም ለመንደፍ ሌላም ነገር ሁሉ ለማድረግ እውቀት አለው፥ እርሱም ከብልሃተኛዎችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር አብሮ ይሁን።
አሁንም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልሃተኞች ጋር አብሮ የሚሆን፥ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ሐምራዊውንና ቀዩን ሰማያዊውንም ግምጃ የሚሠራ፥ ቅርጽንም የሚያውቅ ብልሃተኛ ሰው ላክልኝ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ አስደማሚ ነገርን ተአምራትንም እንደገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።
ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።