1 ተሰሎንቄ 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ቃል ይህን እንላችኋለን፤ እኛ ሕያዋን የሆንነው፥ ጌታም እስኪመጣ ድረስ የምንቀረው ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህን ነው፤ እኛ በሕይወት ያለንና ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጌታ በተቀበልነው ቃል መሠረት የምንነግራችሁ ይህ ነው፤ ጌታ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሕያዋን ሆነን የምንቈይ የሞቱትን አንቀድምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ |
ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተሰብህ መቃብር አይቀበርም።’”
የነቢያት ወገን የሆነ አንድ ነቢይ በጌታ ታዞ የእርሱ ጓደኛ የሆነውን ሌላ ነቢይ “ምታኝ!” አለው። ነቢዩ ግን እርሱን ለመምታት አልፈቀደም።
“ይከፍላል” አለ። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ሆይ! ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸው? ወይስ ከሌሎች?” አለው።
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! አንቀላፍተው ስላሉት፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ልታዝኑ እንደማይገባ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።