ጌታ ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ሀብታም ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ ድኻ ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 17:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን፦ “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የጌታም ቃል ኪዳን ታቦት በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፣ ነቢዩ ናታንን “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት በዚህ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ነበር፤ አንድ ቀን ንጉሡ ነቢዩን ናታንን አስጠርቶ “እነሆ እኔ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ቤት እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታንን፥ “እነሆ፥ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጣለች” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጦአል፤” አለው። |
ጌታ ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ሀብታም ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ ድኻ ነበረ።
ከዚያም የጌታን ታቦት አምጥተው፥ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ በተዘጋጀለት ስፍራ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ።
ለንጉሡም፦ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቷል” ብለው ነገሩት፥ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግምባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ።
ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፥ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕትም በጌታ ፊት አቀረቡ።
እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና።
ንጉሡም ዳዊት ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ! ስሙኝ፤ ለጌታ ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን የማረፍያ ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤያለሁ፤ ለግንባታም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤
የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።
በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ ይበላና ይጠጣ ፍርድንና ጽድቅን ያደርግ አልነበረምን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር።
እናንተ ብዙ ነገርን ፈልጋችሁ፥ እነሆ ጥቂት ሆነ፤ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። በምን ምክንያት? ይላል የሠራዊት ጌታ። ምክንያቱም እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ስለፈረሰ ነው።