መዝሙር 101:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥ በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣ አጠፋዋለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣ እርሱን አልታገሠውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን በሹክሹክታ የሚያማውን ሰው ዝም አሰኛለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ትምክሕተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ ሥጋዬ በአጥንቶቼ ላይ ተጣበቀ። |
ከዚያኛው ይልቅ ይህ ሰው ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ እላችኋለሁ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላልና፥ ራሱን ግን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል።”
አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ስግብግብ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ።
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤