Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ጢሞቴዎስ 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲሁም ሴቶች መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ሐሜተኞች ያልሆኑ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንዲሁ ሴቶችም የተከበሩ፣ ሐሜተኞች ያልሆኑ ነገር ግን ልከኞችና በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንዲሁም ሚስቶቻቸው የተከበሩ፥ ሰውን የማያሙ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በሁሉም ነገር ታማኞች መሆን ይገባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ጢሞቴዎስ 3:11
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤


እንዲሁም ማንንም የማይሰድቡ፥ ጠበኛ ያልሆኑ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ በጽኑ አስገንዝባቸው።


እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ በሥርዓት የሚሠራ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል።


ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይቈጣጠሩ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥


ጥላቻን የሚከድን ሐሰተኛ ከንፈር አለው፥ ሐሜትንም የሚገልጥ አላዋቂ ነው።


አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፤ መከራን በትዕግስት ተቀበል፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህን ሙሉ ለሙሉ ፈጽም።


የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቋቸው፤ ይልቁንስ ከበፊት ይልቅ ያገልግሏቸው ምክንያቱም በመልካም ሥራቸው የሚጠቀሙት አማኞችና ወዳጆቻቸው ናቸውና። እነዚህን ነገርች አስተምርና ምከር።


ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ብርታት የሰጠኝን ጌታችንን ክርስቶስ ኢየሱስን አመሰግናለሁ፤


ኢየሱስም “እኔ እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጫችሁ የለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው፤” ብሎ መለሰላቸው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በዲያብሎስ እንዲፈተን መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው።


መበለቲቱንና የተፈታችውን ለሚስትነት አይውሰዱ፤ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር የሆነችውን ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረችውን መበለት ይውሰዱ።


ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።


ለላኩት የታመነ መልእክተኛ፥ በመከር ወራት ደስ እንዲሚያሰኝ የውርጭ ጠል ነው፥ የጌታውን ነፍስ ያሳርፋልና።


ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥ በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።


ተቀምጠህ በወንድምህን ላይ ክፉን ተናገርህ፥ የእናትህንም ልጅ አማህ።


በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ የሚቀርቡትን የማይሰድብ።


ካህኑ ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና አመንዝራይቱን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም በባልዋ የተፈታችውን አያግባ።


በዐመፃ፥ በግፍ፥ በስስት፥ በክፋት፥ በቅናት፥ ነፍስ በመግደል፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በተንኮል የተሞሉ፥ የሚያሾከሹኩ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች