እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
ዘኍል 10:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን እንዲህ አለው፦ “ጌታ፦ ‘ለእናንተ እሰጣችኋለሁ’ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ ጌታ ለእስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሙሴ የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፣ “እነሆ፤ እግዚአብሔር፣ ‘እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ጕዞ ጀምረናል፤ በመልካም ሁኔታ ስለምናኖርህ ከእኛ ጋራ ሂድ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል በጎ ነገር ለማድረግ ቃል ገብቷልና አለው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ፥ ሆባብን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊሰጠን ቃል ወደገባልን ምድር ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያበለጽግ ቃል ገብቶልናል፤ ስለዚህ አንተም ከእኛ ጋር አብረህ ሂድ፤ መልካም እናደርግልሃለን” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፥ “እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
የሙሴ አማት ይትሮም የሚቃጠል ቊርባንና መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሊመገቡ ከሙሴ አማት ጋር መጡ።
ሙሴም የምድያን ካህን የሆነውን የአማቹን የይትሮን በጎች ያሰማራ ነበር፤ በጎቹን ከምድረ በዳው ማዶ ነዳቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።
ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ከጌታ ጋር በአንድነት እንሁን፥ ብለው ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ።
ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?
በዚችም የእግር ጫማ ስንኳ የሚያህል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ልጅ ሳይኖረው ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ ሰጠው።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።
የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።
በዚያን ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፥ ዐማች የአባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ባሉጥ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።
እርሱም ቄናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።