ዘፀአት 18:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 የሙሴ አማት ይትሮም የሚቃጠል ቊርባንና መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሊመገቡ ከሙሴ አማት ጋር መጡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ከዚያም የሙሴ ዐማት ዮቶር የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌሎች መሥዋዕቶች ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ አሮንም ከሙሴ ዐማት ጋራ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ለመብላት ከእስራኤል አለቆች ሁሉ ጋራ መጣ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ከዚህም በኋላ የትሮ የሙሴ ዐማት በሙሉ የሚቃጠል ቊርባንና ሌላም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል አለቆችም ሁሉ የተቀደሰውን ምግብ በአምልኮት ሥርዓት በእግዚአብሔር ፊት ለመመገብ ከሙሴ ዐማት ጋር መጡ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 የሙሴ አማት ዮቶርም የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እንጀራ ሊበሉ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 የሙሴ አማት ዮቶርም የሚቃጠል መስዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እንጀራ ሊበሉ አሮን የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ። ምዕራፉን ተመልከት |