ዘፀአት 18:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የምድያን ካህን የሙሴ አማት ይትሮ እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ ጌታም እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣ ሰማ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የምድያም ካህን የሙሴ ዐማት ዮቶር፣ እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገላቸውን ሁሉ እንዲሁም እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብጽ እንዴት እንዳወጣቸው ሰማ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የምድያም ካህን የሆነው የሙሴ ዐማት የትሮ፥ እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር መርቶ ባወጣቸው ጊዜ ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገላቸውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የምድያም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን ከግብፅ እንደ አወጣ ሰማ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 የምድያምም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን ከግብፅ እንዳወጣ ሰማ። ምዕራፉን ተመልከት |