Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 95:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኑ፥ በጌታ ደስ ይበለን፥ ለመዳናችን ዓለት እልል እንበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤ በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኑ፤ እግዚአብሔርን በመዝሙር እናመስግን! ለመዳናችን አምባም የድል እልልታ እናስተጋባለት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግኑ፤ ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 95:1
36 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዐለት ነበር፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።


ለመዘምራን አለቃ፥ በዋሽንት፥ የአሳፍ መዝሙር።


እስትንፋስ ያለው ሁሉ ጌታን ያወድስ። ሃሌ ሉያ።


ጌታ ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤ የመዳኔ ዓለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።


ማርያምም፦ “ለጌታ ዘምሩ በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ” እያለች ዘመረችላቸው።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


የምስጋና መዝሙር። ምድር ሁሉ፥ ለጌታ እልል በሉ፥


ነፍሴ በጌታ ትከብራለች፥ ገሮችም ሰምተው ደስ ይላቸዋል።


ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።


የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤


አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን ባርኩ፥ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።


“ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፥ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፥ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፥ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።


የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤


ከፊቱ ይሄዱ የነበሩትና ይከተሉት የነበሩት ሕዝብ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።


ሃሌ ሉያ! ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና።


ሃሌ ሉያ! አሕዛብ ሁላችሁ፥ ጌታን አመስግኑት፥ ሕዝቦችም በሙሉ አመስግኑት፥


በዚያን ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለጌታ ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ “ለጌታ እዘምራለሁ በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።


ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥


ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥


ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥


የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ።


እጁን በባሕር ላይ ቀኙንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።


በዙፋኑም ፊት፥ በአራቱም ሕያዋን ፍጡራንና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያንን ቅኔ ማንም ሊማረው አልቻለም።


በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ጌታ ቤት ገቡ።


ጌታ ሕያው ነው፥ አምላኬም መጠጊያዬ ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች