በችግር ወይም በግድ ሰው ሁሉ ተገዝትዋልና ይህ ለሰው መሰናክልን ሆነ፤ ከእነርሱ ጋር አንድነት የሌለውን የፈጣሪን ስም ለሚጠቀሙባቸው ለድንጋይና እንጨት አድርገውታልና።
በዚህ ዓይነት በመጥፎ ዕድል ወይም በኃይል ተፅዕኖ የከበረውን የእግዚአብሔር ስም ለድንጋይና ለእንጨት በሰጡ ጊዜ የሰዎች ሕይወት በወጥመድ ገባች።