ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤
ሩት 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ወደ መሬት ዝቅ ብላ እጅ ነሣችው። እርሷም፣ “ባይተዋር የሆንሁትን እኔን ታስበኝ ዘንድ በፊትህ ሞገስ ለማግኘት የበቃሁት እንዴት ነው?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ “እኔ ባዕድ ሆኜ ሳለሁ፥ ስለ እኔ ታስብ ዘንድ፥ እንዴት በፊትህ ሞገስ አገኘሁ?” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ግንባርዋ መሬት እስኪነካ ድረስ እጅ ነሥታ “እኔ ባዕድ ሆኜ ሳለ ስለ እኔ ታስብ ዘንድ እንዴት በፊትህ ሞገስ ላገኝ ቻልኩ?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት “እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን?” አለችው። |
ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤
የአባቴ ቤት ሁሉ በጌታዬ በንጉሥ ዘንድ ሞት የሚገባቸው ነበሩ፤ አንተ ግን እኔን ባሪያህን በገበታህ በሚበሉ መካከል አስቀመጥኸኝ፤ ለንጉሥ ደግሞ ለመናገር ምን መብት አለኝ?”
ንጉሡ ዳዊትም ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?
እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና፤ ወደ እናንተ የመጣ እንግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁንላችሁ፤ እርሱን እንደ ራሳችሁ ውደዱት፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ ተዋደዱ፤ የምትራሩም ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ መምህሮቻችሁንም አክብሩ።
ቦዔዝም፦ ባልሽ ከሞተ በኋላ አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሽ ቀድሞ ወደማታውቂው ሕዝብ እንደ መጣሽ፥ ለአማትሽ ያደረግሽውን ነገር ሁሉ ፈጽሞ ሰምቻለሁ።
እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።
አማትዋም፦ ዛሬ ወዴት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን አለቻት። እርስዋም፦ ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማትዋ ነገረቻት።
ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።
ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፥ ተከተያቸውም፣ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፣ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውኃ ጠጪ አላት።
አቤግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፤ በዳዊትም ፊት በግንባርዋ ወደቀች፤ ምድርም ነክታ ሰገደችለት።