ኤቲም ለንጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! በጌታዬም በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ! ጌታዬ ባለበት ስፍራ ሁሉ፥ በሞትም ቢሆን በሕይወትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገልጋይህ እሆናለሁ” አለው።
ሩት 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሩትም፦ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፣ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፣ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሩት ግን እንዲህ አለች፤ “ተለይቼሽ እንድቀር ወይም እንድመለስ አትለማመጭኝ፤ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምትኖሪበትም እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሩት ግን እንዲህ አለች፦ “እንድተውሽ ተለይቼሽም እንድመለስ አታስገድጅኝ፤ በምትሄጅበት እሄዳለሁ፥ በምታድሪበትም አድራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ተለይቼሽ እንድመለስ አታስገድጅኝ! አንቺ ወደምትሄጂበት ሁሉ እሄዳለሁ፤ አንቺ በምትኖሪበት እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሩትም “ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፤ ሕዘሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤ |
ኤቲም ለንጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! በጌታዬም በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ! ጌታዬ ባለበት ስፍራ ሁሉ፥ በሞትም ቢሆን በሕይወትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገልጋይህ እሆናለሁ” አለው።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፤ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፤ በሀገራቸውም ያርፋሉ፤ መጻተኞችም ከእነርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጨመራሉ።
ሰማይን ያጸናሁ፥ ምድርንም የፈጠርሁ፥ እጆችም የሰማይ ሠራዊትን ያቆሙ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንዳትከተላቸውም እነርሱን አላሳየሁህም። ከግብፅ ምድርም ያወጣሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አትወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚያድንህ የለምና።
የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።
ጴጥሮስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን አሁን ልከተልህ አልችልም? እኔ ነፍሴንም እንኳ ቢሆን ስለ አንተ አሳልፌ እሰጣለሁ” አለው።
ጳውሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? እያለቀሳችሁ ልቤን ትሰብሩታላችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማደርገው መከራንና እግር ብረትን ብቻ አይደለም፤ እኔ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞትም ቢሆን የቈረጥሁ ነኝ” አለ።
እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሣውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ ይናገራሉ።
እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ፥ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞሬዎናውያንን ከፊታችን አሳደደ፤ ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና እኛ እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።
በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፣ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች።