La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እናን ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ሠርቶ እንደ ፈጸመ ሰው ያደ​ር​ገን ዘንድ፤ ይህም በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ ጸን​ተው ለሚ​ኖሩ ነው እንጂ በሥጋ ሕግ ለሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይኸውም በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ በምንመላለስ በእኛ፣ ሕጉ የሚጠይቀው ጽድቅ ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸም ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንደ ሥጋ ሳይሆን እንደ መንፈስ በምንመላለስ በእኛ፥ ሕጉ የሚጠይቀው ጽድቅ እንዲፈጸም ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም ያደረገው በሥጋ ፈቃድ ሳይሆን በመንፈስ ፈቃድ በምንመላለስ በእኛ ትክክለኛው የሕግ ትእዛዝ እንዲፈጸም ነው።

Ver Capítulo



ሮሜ 8:4
13 Referencias Cruzadas  

ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


አንተ ሳት​ገ​ዘር ብት​ኖር፥ ኦሪ​ት​ንም ብት​ጠ​ብቅ አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ መገ​ዘር ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች።


እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ኦሪ​ትን እን​ሽ​ራ​ለን? አን​ሽ​ርም፤ ኦሪ​ትን እና​ጸ​ና​ለን እንጂ።


ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እሠ​ራ​ለሁ፤ በሥ​ጋዊ ሥር​ዐ​ትም እን​ደ​ም​ን​ኖር አድ​ር​ገው በሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩን ሰዎች ላይ በድ​ፍ​ረት ለመ​ና​ገር አስ​ባ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን በዚህ ዓይ​ነት ድፍ​ረት እን​ድ​ና​ገር እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጉኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ።


በሥ​ጋ​ች​ንስ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን በእ​ር​ሱው ሥር​ዐት የም​ን​ሄ​ድና የም​ን​ዋጋ አይ​ደ​ለም።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈስ ኑሩ እንጂ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ አታ​ድ​ርጉ።


አሁን ግን በፊቱ ለመ​ቆም የተ​መ​ረ​ጣ​ች​ሁና ንጹ​ሓን፥ ቅዱ​ሳ​ንም ያደ​ር​ጋ​ችሁ ዘንድ በሥ​ጋው ሰው​ነት በሞቱ ይቅር አላ​ችሁ።


ስማ​ቸው በሰ​ማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅ​በረ በኵ​ርም፥ ሁሉን ወደ​ሚ​ገ​ዛም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ወደ ፍጹ​ማን ጻድ​ቃ​ንም ነፍ​ሳት፥


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።


ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤


በአፋቸውም ውሸት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውም።