ሮሜ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደ ነገሠ ሁሉ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ እንዲነግሥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የሆነው፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘለዓለም ሕይወት፥ በጽድቅ በኩል እንዲነግሥ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው በሞት ምክንያት ኃጢአት እንደ ነገሠ ሁሉ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን በመስጠት ይነግሣል። |
አብርሃም፥ ዘሩም ዓለምን ይወርስ ዘንድ ተስፋ ያገኘ የኦሪትን ሥራ በመሥራት አይደለም፤ በእግዚአብሔር ቃል፥ እርሱንም በማመን በእውነተና ሃይማኖቱ ይህን አገኘ እንጂ።
ስለዚህም በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ፤ እንደዚሁም ሁሉ ኀጢአትን ስለ አደረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ።
ነገር ግን በአዳም ኀጢአት ምክንያት ከአዳም እስከ ሙሴ የበደሉትንም ያልበደሉትንም ሞት ገዛቸው፤ ሁሉ በአዳም አምሳል ተፈጥሮአልና፥ አዳምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።
የአንዱ ሰው ኀጢአት ሞትን ካነገሠችው በአንድ ሰው በደልም ሞት ከገዛን፥ የአንዱ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ የጸጋው ብዛትና የጽድቁ ስጦታ እንዴት እጅግ ያጸድቀን ይሆን? የዘለዓለም ሕይወትንስ እንዴት ያበዛልን ይሆን?
ለምትታዘዙለት፥ እሺ ለምትሉትም እናንተ አገልጋዮች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ለተባበራችሁለትስ ራሳችሁን እንደ አስገዛችሁ አታውቁምን? ኀጢአትንም እሺ ብትሉአት፥ ተባብራችሁም ብትበድሉ እናንት ለሞት ተገዢዎች ትሆናላችሁ፤ ጽድቅንም እሺ ብትሉአት ለበጎ ሥራም ብትተባበሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁ።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችሁማል፤ ያበረታችሁማል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤