ከእኔ ጋር በሥራ የሚተባበረው ጢሞቴዎስም፥ ከዘመዶች ወገን የሚሆኑ ሉቅዮስም፥ ኢያሶንም፥ ሱሲ ጴጥሮስም ሰላም ይሉአችኋል።
ሮሜ 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክርስቶስን ሥራ በመሥራት የምንተባበረውን ኡሩባኖስን፥ ወዳጄ ስንጣክንንም ሰላም በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክርስቶስ ዐብሮን ለሚሠራው ለኢሩባኖንና ለውድ ወዳጄ ለስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራው ለኡርባኖንና ለምወደውም ለስታኺ ሰላምታ አቅርቡልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክርስቶስ ሥራ ተባባሪያችን ለሆነው ለዑርባኖስና ለምወደውም ለእስጣኩስ ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራ ለኢሩባኖን ለምወደውም ለስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
ከእኔ ጋር በሥራ የሚተባበረው ጢሞቴዎስም፥ ከዘመዶች ወገን የሚሆኑ ሉቅዮስም፥ ኢያሶንም፥ ሱሲ ጴጥሮስም ሰላም ይሉአችኋል።
ከዘመዶች ወገን የሚሆኑትን ከእኔ ጋር ያመኑ እንድራናቆስንና ዩልያንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክርስቶስን እንደ አገለገሉ ሐዋርያት ያውቁአቸዋል።
ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረባችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው እርሱ አድሮባችሁ ባለ መንፈሱ ለሟች ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣታል።
በክርስቶስ ያመነ አንድ ሰው አውቃለሁ፤ ዘመኑ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥጋው ይሁን በነፍሱ እንጃ፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ነጥቀው ወሰዱት።
አሁንም አብሮኝ የሚሠራውን ወንድማችንን አፍሮዲጡን ወደ እናንተ ልልከው አስቤአለሁ፤ እርሱም የክርስቶስ ሎሌ ነው፤ ለእናንተም መምህራችሁ ነው፤ ለእኔም ለችግሬ ጊዜ መልእክተኛዬ ነው።