ሮሜ 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቅዱሳንም እንደሚገባ በጌታችን ተቀበሉአት፤ እርስዋ ለብዙዎች፥ ለእኔም ረዳት ናትና፤ ለችግራችሁም በፈቀዳችሁት ቦታ መድቡአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለቅዱሳን ተገቢ በሆነው አቀባበል በጌታ እንድትቀበሏትና ከእናንተም የምትፈልገውን ማንኛውንም ርዳታ እንድታደርጉላት አሳስባችኋለሁ፤ ለብዙ ሰዎችና ለእኔም ጭምር ታላቅ ድጋፍ ነበረችና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀአሉአት፤ ከእናንተም በምትፈልገው በማንኛውም ነገር እርዱአት፤ እርሷ ለብዙዎች ለእኔም ጭምር ረድታለችና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ እኔንና ሌሎችንም ብዙ ሰዎች የረዳች ስለ ሆነች ምእመናን እንግዶችን መቀበል እንደሚገባቸው ዐይነት በጌታ ስም ተቀብላችሁ በሚያስፈልጋት ነገር ሁሉ እንድትረዱአት ዐደራ እላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት። |
ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚያደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ተነሥና ሂድ፤ በአሕዛብና በነገሥታት፥ በእስራኤል ልጆችም ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና።
በኢዮጴ ሀገርም ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ በትርጓሜውም ዶርቃስ ይሉአታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እርስዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽዋትም ትሰጥ ነበር።
ጴጥሮስም ተነሥቶ አብሮአቸው ሄደ፤ በደረሰም ጊዜ ወደ ሰገነት አወጡት፤ ባልቴቶችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለቅሱላትም ነበር፤ ዶርቃስም በሕይወት ሳለች የሠራችውን ቀሚሱንና መጐናጸፊያውን አሳዩት።
እኔንና አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ በእንግድነት የተቀበለ ጋይዮስም ሰላም ብሎአችኋል፤ የከተማው መጋቢ አርስጦስና ወንድማችን ቁአስጥሮስም ሰላም ብለዋችኋል።
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።
ከእኔ ጋር የተማረከው አርስጥሮኮስ፥ ወደ እናንተ በሚመጣ ጊዜ ትቀበሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘዝኋችሁ የበርናባስ የአባቱ ወንድም ልጅ ማርቆስም፥
እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤