ሮሜ 15:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ለማድረግ የአባቶቻችንንም ተስፋ ያጸና ዘንድ ለግዝረት መልእክተና ሆነ እላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ለእግዚአብሔር እውነት ሲል ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ እንደ ሆነ እነግራችኋለሁና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ሊያጸና፤ ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ ለተገረዙት አገልጋይ ሆነ እላለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ስናገር እግዚአብሔር ለቀደሙት አባቶች የሰጠው ተስፋ እንዲፈጸምና የእግዚአብሔርም እውነተኛነት እንዲታወቅ ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ ሆነ ማለቴ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ደግሞም፦ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ ለስምህም እዘምራለሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ አሕዛብ ስለ ምሕረቱ እግዚአብሔርን ያከብሩ ዘንድ፥ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውነት የመገረዝ አገልጋይ ሆነ እላለሁ። |
ከዚህ ቦታ ያይደሉ ሌሎች በጎችም አሉኝ፤ እነርሱንም ወደዚህ አመጣቸው ዘንድ ይገባኛል፤ ቃሌንም ይሰሙኛል፤ ለአንድ እረኛም አንድ መንጋ ይሆናሉ።
ጳውሎስና በርናባስም ደፍረው እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ለእናንተ አስቀድሞ ልንነግራችሁ ይገባል፤ እንቢ ብትሉና ራሳችሁን ለዘለዓለም ሕይወት የተዘጋጀ ባታደርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕዛብ እንመለሳለን።
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ርኅራኄውንና ጭካኔውን አስተውል፤ የወደቁትን ቀጣቸው፤ አንተን ግን ይቅር እንዳለህ ብትኖር ማረህ፤ ያለዚያ ግን አንተም ትቈረጣለህ።
በአሕዛብ መካከል ኢየሱስ ክርስቶስን አገለግል ዘንድ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትምህርት አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተወደደና የተመረጠ መሥዋዕት ይሆኑ ዘንድ።
እግዚአብሔር ታጋሽ በመሆኑ፥ እሺ በማለቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም የሚያምኑትን እንደሚያጸድቃቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው።
ስለዚህም እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጠው ተስፋ የታመነ ይሆን ዘንድ፥ የሚጸድቁ በእምነት እንጂ የኦሪትን ሥራ በመፈጸም ብቻ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ጽድቅን በእምነት አደረገ።
እነሆ፥ እርስ በርሳችሁ፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔ የአጵሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክርስቶስ ነኝ” የምትሉትን እነግራችኋለሁ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ይህን እንነግራችኋለን፦ ሥጋዊና ደማዊ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም፥ የሚፈርሰው የማይፈርሰውን አይወርስም።
እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ሁሉ በክርስቶስ እውነት ሆኖአልና፤ ስለዚህም በእርሱ ለእግዚአብሔር ክብር አሜን እንላለን።
ያንጊዜ ክርስቶስን አታውቁትም ነበር፤ ከእስራኤል ሕግ የተለያችሁ ነበራችሁ፤ ከተስፋው ሥርዐትም እንግዶች ነበራችሁ፤ ተስፋም አልነበራችሁም፤ በዚህም ዓለም እግዚአብሔርን አታውቁትም ነበር።