Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ወደ ወገ​ኖቹ መጣ፤ ወገ​ኖቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ወደ ራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፤ ነገር ግን የገዛ ወገኖቹ አልተቀበሉትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ወደ ወገኖቹ መጣ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 1:11
17 Referencias Cruzadas  

የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ።


ባየ​ውና በሰ​ማው ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን የሚ​ቀ​በ​ለው የለም።


እርሱም መልሶ “ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም፤” አለ።


እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እው​ነት ለማ​ድ​ረግ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም ተስፋ ያጸና ዘንድ ለግ​ዝ​ረት መል​እ​ክ​ተና ሆነ እላ​ለሁ።


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።


እነ​ር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ችን ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ክር​ስ​ቶስ በሥጋ ተወ​ለደ፤ እር​ሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።


ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።


“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል።


በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሐሰ​ትም አል​ና​ገ​ርም። ሕሊ​ና​ዬም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ናል፤


በዓ​ለም ነበረ፤ ዓለ​ሙም በእ​ርሱ ሆነ፤ ዓለሙ ግን አላ​ወ​ቀ​ውም።


ለተ​ቀ​በ​ሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚ​ያ​ምኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እን​ዲ​ሆኑ ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዝ​ሙ​ሩን፥ “እና​ትህ እነ​ኋት” አለው፤ ከዚ​ያ​ችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝ​ሙሩ ተቀ​ብሎ ወደ ቤቱ ወሰ​ዳት።


እርስ በር​ሳ​ች​ንም ተሳ​ስ​መን ተሰ​ነ​ባ​በ​ትን፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ መር​ከብ ወጣን፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ተመ​ለሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios