La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሚ​ገ​ባስ እና ብር​ቱ​ዎች ደካ​ሞ​ችን በድ​ካ​ማ​ቸው እን​ድ​ን​ረ​ዳ​ቸው ነው፤ ለራ​ሳ​ች​ንም አና​ድላ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛ ብርቱዎች የሆንን፣ የደካሞችን ጕድለት መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኛ ብርቱዎች የሆንን የደካሞችን ድካም መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኛ በእምነት ብርቱዎች የሆንን፥ የደካሞችን ድካም መሸከም ይገባናል እንጂ ራሳችንን ብቻ የምናስደስት መሆን የለብንም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል።

Ver Capítulo



ሮሜ 15:1
13 Referencias Cruzadas  

እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ።


ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈ​ቀ​ደ​ለት የሚ​ያ​ምን ሁሉን ይብላ፤ የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን አት​ክ​ልት ይብላ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያና​ገ​ረ​ለ​ት​ንም ተስፋ ይቀ​ራል ብሎ አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም፤ በእ​ም​ነት ጸና እንጂ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን ሰጠ።


እኛስ ስለ ክር​ስ​ቶስ ብለን አላ​ዋ​ቂ​ዎች ነን፤ እና​ንተ ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ጠቢ​ባን ናችሁ፤ እኛ ደካ​ሞች ነን፤ እና​ንተ ግን ብር​ቱ​ዎች ናችሁ፤ እና​ንተ ክቡ​ራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተ​ዋ​ረ​ድን ነን።


ደካ​ሞ​ች​ንም እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለደ​ካ​ሞች እንደ ደካማ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ በሁሉ መን​ገድ አን​ዳ​ን​ዶ​ቹን አድን ዘንድ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነ​ርሱ ሆንሁ።


ስለ​ዚ​ህም ስለ ክር​ስ​ቶስ መከራ መቀ​በ​ልን፥ መሰ​ደ​ብን፥ መጨ​ነ​ቅን፥ መሰ​ደ​ድን፥ መቸ​ገ​ር​ንም ወደ​ድሁ፤ መከራ በተ​ቀ​በ​ልሁ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ እበ​ረ​ታ​ለ​ሁና።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።


ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም እንጂ ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ብቻ አታ​ስቡ።


ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።


እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።


አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።