Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ደካ​ሞ​ች​ንም እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለደ​ካ​ሞች እንደ ደካማ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ በሁሉ መን​ገድ አን​ዳ​ን​ዶ​ቹን አድን ዘንድ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነ​ርሱ ሆንሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ደካሞችን እመልስ ዘንድ፣ ከደካሞች ጋራ እንደ ደካማ ሆንሁ። በሚቻለኝ ሁሉ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፣ ከሁሉም ጋራ ሁሉን ነገር ሆንሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ደካሞችን መጥቀም እንድችል ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንኩ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በእምነት ደካሞች የሆኑትን ለማዳን ስል እንደ ደካሞች ደካማ ሆንኩ፤ በተቻለ መጠን ጥቂቶችን ለማዳን ከሁሉም ጋር ሁሉን ነገር ሆንኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 9:22
12 Referencias Cruzadas  

ይህም በዚህ ዘመ​ዶ​ችን አስ​ቀ​ና​ቸው እንደ ሆነ፥ ከእ​ነ​ርሱ ወገን የሆ​ኑ​ት​ንም አድን እንደ ሆነ ነው።


እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ።


ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈ​ቀ​ደ​ለት የሚ​ያ​ምን ሁሉን ይብላ፤ የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን አት​ክ​ልት ይብላ።


የሚ​ገ​ባስ እና ብር​ቱ​ዎች ደካ​ሞ​ችን በድ​ካ​ማ​ቸው እን​ድ​ን​ረ​ዳ​ቸው ነው፤ ለራ​ሳ​ች​ንም አና​ድላ።


ሁላ​ች​ንም በእ​ው​ነ​ትና በመ​ል​ካም ሥራ ይታ​ነጽ ዘንድ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችን እና​ድላ።


እኔም ሁሉን በሁሉ ነገር ደስ እን​ዳ​ሰኝ ይድኑ ዘንድ የብ​ዙ​ዎ​ችን ተድላ እሻ​ለሁ እንጂ የራ​ሴን ተድላ የምሻ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና።


ሚስ​ትም ባል​ዋን ታድ​ነው እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምና፤ ባልም ሚስ​ቱን ያድ​ናት እንደ ሆነ አያ​ው​ቅ​ምና።


ነገር ግን በመ​ብል ምክ​ን​ያት ወን​ድሜ የሚ​ሰ​ና​ከል ከሆነ ወን​ድ​ሜን እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥጋን አል​በ​ላም።


እኔ ከሁሉ ይልቅ ነጻ ስሆን ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት እሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ዘንድ እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስ​ገ​ዛሁ።


በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት አን​ድ​ነት ይኖ​ረኝ ዘንድ ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት ሁሉን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ታሞ እኔ የማ​ላ​ዝ​ን​ለት ማን ነው? በድ​ሎስ እኔ የማ​ል​ደ​ነ​ግ​ጥ​ለት ማን ነው?


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos