ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፤ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እንቦሳ ምሰል።
ሮሜ 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌሊቱ አልፎአል፤ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማን ሥራ ከእና እናርቅ፤ የብርሃንንም ጋሻ ጦር እንልበስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሊቱ ሊያልፍ፣ ቀኑም ሊጀምር ነው። ስለዚህ የጨለማን ሥራ ጥለን፣ የብርሃንን ጦር ዕቃ እንልበስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሊቱ አልፎአል፤ ቀኑም ቀርቧል፤ እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን የጦር መሣሪያ እንልበስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊቱ እያለፈ ነው፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ ስለዚህ በጨለማ የሚሠራውን ሥራ እንተው፤ የብርሃንን የጦር መሣሪያ እንልበስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። |
ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፤ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እንቦሳ ምሰል።
በዚያም ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል።
በብርም ወደ ተለበጡ፥ በወርቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖታቱ እንሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያንጊዜ እንደ ትቢያ የደቀቁ ይሆናሉ፤ እንደ ውኃም ይደፈርሳሉ፤ በእነርሱም ጥራጊዎችን ይጥሉባቸዋል።
ነገር ግን ወንድሞቻችን እንዲህ ይቀናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያልፍ ቀርቦአልና፤ አሁንም ያገቡ እንዳላገቡ ይሆናሉ።
ሌሎች ልማድ አድርገው እንደ ያዙት ማኅበራችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ፥ የኀጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።
ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።