ራእይ 19:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግመውም “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እንዲህ አሉ፤ “ሃሌ ሉያ! ጢስ ከርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግመውም እንዲህ አሉ፦ “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይወጣል፤” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም፥ “ሃሌ ሉያ! ከእርስዋ የሚነሣው ጢስ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል!” እያሉ ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግመውም፦ ሃሌ ሉያ አሉ፤ ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል። |
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”
ከዚህ በኋላ በሰማይ “ሃሌ ሉያ! በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው፤” ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።