ራእይ 15:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኀይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤተ መቅደሱም ከእግዚአብሔር ክብር፣ ከኀይሉም በወጣው ጢስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባት መቅሠፍቶች እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤተ መቅደሱ ከእግዚአብሔር ክብርና ከኀይሉ የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ መቅደሱ መግባት አልቻለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተ መቅደሱም ከእግዚአብሔር ክብርና ኀይል የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላእክት የያዙአቸው ሰባት መቅሠፍቶች እስከ ተፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኃይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፥ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም። |
እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጽመው ደነገጡ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም።
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።