ራእይ 14:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላም ሁለተኛ መልአክ፣ “ሕዝቦች ሁሉ፣ የዝሙቷን ቍጣ ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ ከዝሙትዋ የቁጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላም ሁለተኛው መልአክ “የሚያሰክረውን የዝሙትዋን ወይን ጠጅ ለሕዝቦች ሁሉ ያጠጣች ያቺ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ የመጀመሪያውን መልአክ ተከተለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌላም ሁለተኛ መልአክ፦ አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች እያለ ተከተለው። |
እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፤ አትነሣምም በል።” የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው።
ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?
ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።