ራእይ 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አየሁም፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አየሁም፤ እነሆ፤ በፊቴ ነጭ ደመና ነበረ፤ በደመናውም ላይ፣ “የሰውን ልጅ የሚመስል” ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል ደፍቶ፣ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አየሁ፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰው ልጅን የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ፥ ነጭ ደመና አየሁ፤ በደመናው ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል አድርጎአል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አየሁም፥ እነሆም ነጭ ደመና፥ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፥ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው። |
ስለ ግብፅ የተነገረ ራእይ። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም የእጆቻቸው ሥራዎች በፊቱ ይዋረዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።
በራሳቸውም በላይ ከአለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፤ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ።
ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን “እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ፤” እላለሁ’ አለ።”
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ጭኖ እናየዋለን።
ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፤
ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ “ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ትልቁን ኀይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤