La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ራእይ 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው፤ አትጻፈውም፤” የሚል ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰባቱ ነጐድጓዶች በተናገሩ ጊዜ፣ ለመጻፍ ተዘጋጀሁ፤ ነገር ግን፣ “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን በማኅተም ዝጋው እንጂ አትጻፍ” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው፤ አትጻፈውም፤” የሚል ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ እኔ ልጽፍ አሰብኩ፤ ነገር ግን “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን አሽገህ በምሥጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው!” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo



ራእይ 10:4
13 Referencias Cruzadas  

ይህም ሁሉ ነገር እንደ ታተመ መጽ​ሐፍ ቃል ሆኖ​ባ​ቸ​ዋል፤ ማን​በ​ብ​ንም ለሚ​ያ​ውቅ፥ “ይህን አን​ብብ” ብለው በሰ​ጡት ጊዜ እርሱ፥ “ታት​ሟ​ልና ማን​በብ አል​ች​ልም” ይላ​ቸ​ዋል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ታላቅ አዲስ ሰሌዳ ወስ​ደህ፦ ‘ቸኩ​ለህ ማርክ፤ ፈጥ​ነ​ህም በዝ​ብዝ’ ብለህ በሰው ብርዕ ጻፍ​በት።


እን​ዳ​ይ​ማ​ሩ​አት ሕግን የሚ​ያ​ጠ​ፉ​አት ሰዎች ያን​ጊዜ ይገ​ለ​ጣሉ።


“ምስ​ጢሩ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የተ​ገ​ለ​ጠው ግን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው።


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።


እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።


ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና ሲናገረኝና “ሂድና በባሕርና በምድር ላይ ከሚቆመው መልአክ በእጁ ያለችውን የተከፈተችውን መጽሐፍ ውሰድ፤” ሲል ሰማሁ።


ለእኔም “ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።