La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ራእይ 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመቅረዞቹም መካከል “የሰው ልጅ የሚመስል” አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ የሚደርስ መጐናጸፊያ የለበሰ፣ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመቅረዞቹ መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱ እስከ እግሩ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰ፥ ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።

Ver Capítulo



ራእይ 1:13
15 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እር​ስ​ዋን ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም፥ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም እንደ ሠሩ የል​ብሰ መት​ከ​ፉን ቋድ ሠሩ።


ወገ​ቡን በጽ​ድቅ ይታ​ጠ​ቃል፤ እው​ነ​ት​ንም በጎኑ ይጐ​ና​ጸ​ፋል።


እጀ ጠባ​ብም አለ​በ​ሰው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ስም አለ​በ​ሰው፤ ልብሰ መት​ከ​ፍም ደረ​በ​ለት፤ በል​ብሰ መት​ከ​ፉም አሠ​ራር ላይ በብ​ል​ሃት በተ​ጠ​ለፈ ቋድ አስ​ታ​ጠ​ቀ​ውና በእ​ርሱ ላይ አሰ​ረው።


ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።


አየሁም፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።


ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ጥሩ የጌጥ ልብስ ለበሱ፤ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ።


“በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦