የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
መዝሙር 98:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ በሥራቸው ሁሉ ግን ትበቀላቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፣ ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥ ተራሮችም በደስታ ይዘምሩ፥ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ወንዞች አጨብጭቡ፤ እናንተ ተራራዎች በእግዚአብሔር ፊት እልል እያላችሁ በአንድነት ዘምሩ። |
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሐሤትም ትማራላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በደስታ ሊቀበሏችሁ ይዘላሉ፤ የሜዳም ዛፎች ሁሉ በቅርንጫፎቻቸው ያጨበጭባሉ።