አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።
ክፉዎች እስከ መቼ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎች እስከ መቼ ይፈነጫሉ?
አቤቱ፥ ክፉዎች እስከ መቼ? ክፉዎች እስከ መቼ ይኮራሉ?
ክፉዎች የሚታበዩት እስከ መቼ ነው? እግዚአብሔር ሆይ! ኧረ እስከ መቼ ነው?
የኀጢኣተኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝንጉዎችም ደስታ ጥፋት ነው።
እጅህ ጠላትን አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤ አሕዛብን አሠቃየኻቸው፥ አሳደድኻቸውም።
አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው አሉ፦ “ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓላት ከምድር እንሻር
የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ።
ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና።
አንተ የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ! ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ፤ ጸጥ ብለህም ዕረፍ።
አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም።
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።