Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 94:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ክፉዎች እስከ መቼ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎች እስከ መቼ ይፈነጫሉ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አቤቱ፥ ክፉዎች እስከ መቼ? ክፉዎች እስከ መቼ ይኮራሉ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ክፉዎች የሚታበዩት እስከ መቼ ነው? እግዚአብሔር ሆይ! ኧረ እስከ መቼ ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነውና፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 94:3
16 Referencias Cruzadas  

እነርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ሁሉን የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ አትፈርድም? እስከ መቼስ ደማችንን በምድር በሚኖሩት ላይ አትበቀልም?” አሉ።


የኀጢአተኞች መፈንጨት ለዐጭር ጊዜ፣ የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?


በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ።


አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣ ለምን ተውኸኝ? ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?


“ ‘ወዮ! የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፤ የማታርፈው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤ ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን? ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው?


የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነድደው፣ እስከ መቼ ድረስ ነው?


እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ነው? የምትቈጣውስ ለዘላለም ነውን? ቅናትህስ እንደ እሳት ሲነድድ ይኖራልን?


ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቍጣ በረደ።


አስቴርም፣ “ያ ባላጋራና ጠላት ይህ ክፉው ሐማ ነው” አለች። ከዚያም ሐማ በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት እጅግ ደነገጠ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣ አንተ የማትሰማው፣ “ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣ አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios