አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፤
በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤ የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ።
በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ቅጣት ታያለህ።
ክፉዎች ሲቀጡ በዐይንህ ታያለህ።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
እግዚአብሔርም በዚያ ቀን እስራኤልን ከግብፃውያን እጅ አዳናቸው፤ እስራኤልም ግብፃውያን እንደ ሞቱ በባሕር ዳር አዩ።
እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ይደርስበታል።
ዓይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም፦ እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ።
በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥