ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
መዝሙር 91:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ከዐዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከተሰወሩ ወጥመዶችና ለሞት ከሚያደርሱ በሽታዎች ይጠብቅሃል። |
ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
“በምድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ ቢሆን፥ አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢመጣ፥ የሕዝብህም ጠላት ከከተሞቻቸው በአንዲቱ ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
ኤፍሬም ከእግዚአብሔር ጋር ጉበኛ ነበረ፤ አሁን ግን ነቢዩ በመንገዱ ሁሉ ላይ ክፉ ወጥመድ ሆነ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ርኵሰትን አደረጉ።
ወይስ ወፍ፥ አጥማጅ ከሌለው፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ሳይዝ ከምድር በከንቱ ይፈናጠራልን?
ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።