አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
መዝሙር 90:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሺሕ ዓመት በፊትህ፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣ እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓት ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአንተ አንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ነው፤ አልፎ እንደ ሄደው እንደ ትናንት ነው፤ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው። |
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዐምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፤ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ።
እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
ጌዴዎንም፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት መጀመሪያ ዘብ ጠባቂዎች ሳይነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፤ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮዎች ሰባበሩ፤