ፍርዴንና በቀሌን አድርገህልኛልና፤ የጽድቅ ፈራጅ ሆይ፥ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።
ፍርዴም ጕዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤ ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።
ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፥ ይሰናከላሉ ከፊትህም ይጠፋሉ።
በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጅ ነህ። የእኔንም ጉዳይ በማየት መብቴን ጠብቀህ በቅን ትፈርድልኛለህ።
ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በሰማይ ስማ፤ ፍርድንም አድርግላቸው።
ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
እንደሰማን እንዲሁ አየን፥ በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል።
በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለንና፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።
አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤