የመቅሠፍትህን ኀይል ማን ያውቃል? ከቍጣህ ግርማ የተነሣ አለቁ።
ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤ ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አንተ መሠረትህ።
አንተ ረዓብን እንደ ተገደለ አዋረድኸው፥ በኃያሉ ክንድህ ጠላቶችህን በተንሃቸው።
ሰማይና ምድር የአንተ ናቸው፤ ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ የፈጠርክ አንተ ነህ።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ሰማይና ምድር ዓለማቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
ከሰማይ በታች ያለ የምድርንስ ስፋት አስተውለሃልን? መጠኑም ምን ያህል እንደ ሆነ እስኪ ንገረኝ!
የከሰል እሳት እንደሚቃጠልበት ምድጃ ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
ደስታንና ማዳንህን ስጠኝ፥ በጽኑ መንፈስም አጽናኝ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክንድሽንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድሞውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትውልድ ተነሺ።
“ምድር በመላዋ የእግዚአብሔር ናትና።”
እንግዲህ “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ያላችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገራችሁና ባልንጀራችሁም የሚጠራጠር ስለሆነ አትብሉ።