እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ ለዘለዓለም እንደማታስባቸው በሙታን መካከል የተጣልሁ ሆንሁ፤ እነርሱ ከእጅህ ርቀዋልና።
በርግጥም ስለ ጽዮን፣ “ይህም ያም ሰው በርሷ ውስጥ ተወለዱ፤ ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል።
ስለ ጽዮን ሰው እንዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ በውስጥዋ ተወለደ”፥ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።
ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት ስለ ጽዮን፦ “ይህም ሕዝብ፥ ያም ሕዝብ በእርስዋ ውስጥ ተወልደዋል” ይባላል።
የነፍሱንም ዋጋ ለውጥ፥
በዓለም የደከመ ለዘለዓለም ይድናል፥ ጥፋትን አያይምና።
ዙሪያዋም ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማዪቱ ስም፦ ‘እግዚአብሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠራል።”
እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።
እንግዲህ ስለዚህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይችለናል?
እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤልና ስለ ሌሎች ነቢያት እነግራችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና።