የሕዝብህን ኀጢአት ይቅር አልህ፤ ዐበሳቸውንም ሁሉ ሰወርህ።
ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤ እጅግም ትጓጓለታለች፤ ልቤና ሥጋዬም፣ ለሕያው አምላክ እልል በሉ።
የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!
የቤተ መቅደስህን አደባባይ በጣም እናፍቃለሁ፤ ለሕያው አምላክ በሙሉ ልቤ በደስታ እዘምራለሁ።
እርሱን ወዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ነገሩ ፍጻሜም ምነው በደረስሁ!
መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤ ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ በምድረ በዳ ኀይልና ጽንዐት አምላችኋለሁ፤ ልጅ ወንድሜን ያገኛችሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ትነግሩት ዘንድ።
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ትእዛዝህ በምድር ላይ ብርሃን ነውና ነፍሴ በሌሊት ወደ አንተ ትገሠግሣለች። በምድር የምትኖሩም ጽድቅ መሥራትን ተማሩ።
ሰማይን ብትከፍት ከአንተ የተነሣ ተራሮች ይንቀጠቀጣሉ፤ ይቀልጣሉም።
ያዕቆብ ሆይ፥ ቤቶችህ፥ እስራኤል ሆይ ድንኳኖችህ ምንኛ ያምራሉ!