ለያዕቆብ ያቆመውን ምስክር፥ ለእስራኤልም የሠራውን ሕግ፥ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ለልጆቻቸው ይነግሩ ዘንድ፥
የድሮውን ዘመን አሰብሁ፤ የጥንቶቹን ዓመታት አውጠነጠንሁ።
ዐይኖቼ እንዲተጉ ያዝሃቸው፥ ስለተረበሽኩ አልተናገርሁም።
ስላለፉት ቀኖች አስባለሁ፤ ጥንት ስለ ነበሩት ዓመቶችም አስታውሳለሁ።
እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ ጻድቅ ነው።
አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፥ ውረድም፤ ተራሮችን ዳስሳቸው፥ ይጢሱም።
ልቤ መልካም ነገርን ተናገረ፥ እኔም ሥራዬን ለንጉሥ እናገራለሁ፤ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክንድሽንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድሞውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትውልድ ተነሺ።
የዱሮውን ዘመን አስብ፤ የልጅ ልጅንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ይነግርህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፤ ይተርኩልህማል።